top of page

ወደ ሰላምታ ድረገጽ እንኳን ደህና መጡ!

የሚተማመኑበት የካናዳ ኢሚግሬሽን አገልግሎት ሰጪ

ሰላምታ የኢሚግሬሽን አገልግሎት በካናዳ የንግድ ማህበራት ህግ መሰረት የተቋቋመ የካናዳ የኢሚግሬሽን አማካሪ ድርጅት ነው። የሚገኘው በካልጋሪ፣ አልበርታ ካናዳ ውስጥ ሲሆን የድርጅቱ ባለቤት እና መስራች፣ ሳይን አማኑኤል፣ ሬጉሌትድ የካናዳ ኢሚግሬሽን አማካሪ (RCIC - Regulated Canadian Immigration Consultant) እንዲሁም የካናዳ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አማካሪዎች ኮሌጅ (CICC - College of Immigration and Citizenship Consultants) አባል ናት።

Calgary tower
Syn RCIC-IRB

ሳይን አማኑኤል

Syn April 29 2023.png
Syn Amanuel (RCIC)_edited.png

የቢሮ የሥራ ሰዓት

 ከሰኞ እስከ ሐሙስ 9:00 Am - 5:00 Pm

አርብ 9:00 Am - 1:00 Pm

በበዓል ቀናት እንዲሁም ቅዳሜና እሁድ ዝግ ነው

ወይዘሮ ሳይን በጥሩ አቋም የምትገኝ የCICC አባል በመሆኗ በኢሚግሬሽን እና ስደተኛ ጥበቃ ህግ መሰረት አንድን ግለሰብ ለማማከር እንዲሁም ወክላ ጉዳይ ለማስፈጸም እንድትችል በካናዳ መንግስት ስልጣን ተሰጥቷታል።

ሳይን አማኑኤል ከኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ አማካሪዎች ኮሌጅ (ኮሌጅ) ደረጃዋ ወደ ክፍል L3 RCIC-IRB - ያልተገደበ ፕራክቲስ ከፍ መደረጉን የሚያረጋገጥ የባለሥልጣን ደብዳቤ ተሰጥቷታል። የዚህ ፈቃድ ባለቤት እንደመሆኗ መጠን በኢሚግሬሽን፣ ረፊዩጂ እና ዜግነት ካናዳ IRCC (Immigration Refugees & Citizenship Canada) እንዲሁም በአራቱ የካናዳ ኢሚግሬሽን ስደተኛ ቦርድ ተቋማት (IRB - Immigration and Refugee Board of Canada) ማለትም፤

 • በስደተኞች ክፍል (Immigration Division - ID)

 • በኢሚግሬሽን ይግባኝ ክፍል (Immigration Appeal Division - IAD)

 • ስደተኛ ጥበቃ ክፍል (Refugee Protection Division - RPD) እና

 • ስደተኞች ይግባኝ ክፍል (Refugee Appeal Division - RAD) 

ያለገደብ ደበኞቿን ወክላ ለመቅረብ ትችላለች ማለት ነው።

በካናዳ ህግ/ቢል C-35 በማናቸውም ደረጃ የሚገኝ የኢሚግሬሽን አገልግሎቶችን በክፍያ መስጠት የሚችለው ኦቶራይዝድ ረፕረዘንታቲቭ (Authorized Representative) ብቻ ነው። ኦቶራይዝድ ረፕረዘንታቲቭ የሚከተሉትን ያካትታል:

 • የካናዳ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አማካሪዎች ኮሌጅ - CICC በጥሩ አቋም የሚገኙ አባላት፣

 • በፕሮቪንሺያል ወይም ተሪቶሪያል የህግ ማህበራት በጥሩ አቋም የሚገኙ ጠበቃዎች

 • በኩቤክ ክፍለሃገር ውስጥ በጥሩ አቋም የሚገኙ የChambre des notaires du Quebec አባል የሆኑ ኖታሪዎች።

 • ​በኦንታሪዮ ክፍለሃገር የሚገኙ ፓራሊጋልስ (የህግ ባለሞያዎች)

ስለዚህ ጉዳይ ከካናዳ መንግስት የተሰጠ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘትና ዋና ነጥቦቹን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ። ወይም የህግ/ቢል C-35 ማሻሻያ (Bill C-35: An Act to amend the Immigration and Refugee Protection Act click) ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ።

ስለ ሳይን አማኑኤል
Temporary Resident

ጊዜያዊ ኗሪ

ጊዜያዊ ኗሪ ማለት ለጊዜያዊ ጉዳይ እንደ ጎብኚ፣ ተማሪ፣ ሠራተኛ፣ ወይም ጊዜያዊ ነዋሪ ሆኖ ካናዳ ውስጥ እንዲገቡ እና እንዲቆዩ ሕጋዊ ፈቃድ የተሰጣቸው የውጭ አገር ዜጎች ናቸው። የጊዜያዊ ኗሪዎች ፈቃድ የሚኖራቸው በአካል በካናዳ የሚኖሩ የውጭ አገር ዜጎች ብቻ ናቸው።

Permanent resident

ቋሚ ኗሪ

ቋሚ ነዋሪዎች ወደ ካናዳ በመሰደድ ቋሚ ተቀማጭነት የተሰጣቸውው ነገር ግን የካናዳ ዜጋ ያልሆኑ ሰዎች ናቸው። ቋሚ ነዋሪዎች ነዋሪነታቸውን በካናዳ ያደርጉ  የሌሎች አገሮች ዜጎች ናቸው።

Study in Canada

ካናዳ ውስጥ መማር

በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ብዙ ተማሪዎች ካናዳን የትምህርት ቦታቸው አድርገው ይመርጣሉ ። ካናዳ በትምህርት ጥራቷ ትታወቃለች። የካናዳ ዲግሪ/ዲፕሎማ በመላው ዓለም ተቀባይነቱ ከፍተኛ ነው። በተጨማሪም በካናዳ መማር የተለያዩ የቋሚ ነዋሪነት ማግኘት ለሚቻልባቸው ፕሮግራሞች መንገድ የሚከፍት ነው።

Refugees Immigration

የስደተኞች ኢሚግሬሽን

ካናዳ በአንፃራዊ ሁኔታ ክፍትና በሚገባ ቁጥጥር የሚደረግበት የኢሚግሬሽን ስርዓቷ፣ ለስደተኞችና ለመፃተኞች ዋነኛ መዳረሻ ሆናለች። ባለፈው ግማሽ ምዕተ ዓመት ስደተኞችን በመቀበልና የተለያዩ ባሕሎችን ከፍተኛ ግምት በመስጠት ረገድ ጥሩ ስም አትርፋለች።

Other Services

ሌሎች አገልግሎቶች

የቪዛ ማመልከቻ ድጋፍ፣ ኢሚግሬሽንን የተመለከተ ህጋዊ ምክር፣ የሰነድ ዝግጅት እና ቅንብር እርዳታ፣ በኢሚግሬሽን ቢሮ የተሰጠ ውሳኔን በተመለከተ ይግባኝ  ለማለት  መወከል፣ እንዲሁም የመኖሪያ እና የዜግነት ማመልከቻ ማስገባት እና መከታተል፣ ጉዞ ሰንዶች (ትራቭል ዶኩመንት/ፓስፖርት) እና ለቋሚ ነዋሪ ካርድ ማመልከት እና ሌሎችም

የትምህርት እና ሞያዊ የስራ ልምምዶች

ወ/ሮ ሳይን አማኑኤል በእንግዳ ተቀባይነት፣ በአስተርጓሚነት፣ አዲስ የመጡ እንግዶችን በማገዝና በማላመድ በሚሰሩ የተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ እንዲሁም በግል በፈቃደኛ ሰራተኛነት ወደ ሁለት አስርተ አመታት  የሚጠጋ ልምድ አላት።

ከምታውቃቸው ሰዎች ውስጥ አብዛኞቹ ስደተኛ የነበሩ፣ ጥገኝነት ጠያቂዎች እና በተለያዩ የስደት ምድቦች ወደ ካናዳ የመጡ ግለሰቦች ናቸው።

በ2016 የኢሚግሬሽን ኮንሰልታንት ዲፕሎማ ማግኘቷ የካናዳ ኢሚግሬሽን እንዴት እንደሚሰራ እንዲሁም ውጤታማ የሆኑ ከ60 የሚበልጡ ወደካናዳ  የሚመጣባቸው መንገዶችን በተመለከተ ጥልቅ የሆነ ግንዛቤ አስጨብጧታል።

ሳይን አማኑኤል ከ2016 ጀምሮ ረጉሌትድ የካናዳ ኢሚግሬሽን አማካሪ በመሆን በዚሁ ስራ ላይ ተሰማርታ ትገኛለች።

 

የትምህርት ማስረጃዎች:

 • የኢሚግሬሽን ኮንሰልታንት - ዲፕሎማ (Ashton College)

 • የስደተኛ ስፖንሰርሺፕ የስልጠና መርሃግብር - ሰርተፊኬት - (RSTP)

 • ቃለ መሃላ አስፈጻሚ - ሰርተፊኬት (Commissioner of Oaths)

 • ኖታሪ ፐብሊክ በአልበርታ ውስጥና ለአልበርታ - Notary Public in and for Alberta

 

የፈቃደኛ አገልግሎት:

 • Board of Directors at International Ave BRZ, Calgary (2019-Current) 

 • CIWA (ካልጋሪ፣ አልበርታ) 2008 - 2011

 • SISO (ሃሚልተን፣ ኦንታሪዮ) 2003 -2006

 • New Comers ( ሴይንት ጆን፣ ኒውብረንስዊክ) 2001 – 2003

SAH image_edited.png
ተጨማሪ መረጃዎች

ስደተኞች በግል  ስፖንሰር ሊደረጉባቸው የሚችሉባቸው ሶስት መንገዶች  

 1. ቡድን 5 - በአንድ ከተማ ውስጥ የሚኖሩና ስደተኛውን (ከነቤተሰቡ) ለአንድ አመት ለመደገፍ የሚያስችል የገንዘብ አቅም ያላቸው የካናዳ ዜግነት ወይም የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ኣምስት ሰዎች  *

 2. ኮምዩኒቲ ስፖንሰር  - ማናቸውም የተመዘገቡ የካናዳ ድርጅቶች ወይም የንግድ ድርጅቶች (ኢንኮርፖሬትድ የሆኑም ሆነ ያልሆኑ) ስደተኛውን (ከነቤተሰቡ) ለአንድ አመት ለመደገፍ የሚያስችል የገንዘብ አቅም ያላቸው *

 3. ሳህ Sponsorship Agreement Holder -  ሳህ ስደተኞችን ስፖንሰር ለማድረግ እንዲፈቀድላቸው ከካናዳ መንግስት ጋር ስምምነት የገቡ ኢንኮርፖሬትድ ድርጅቶች ናቸው #

ማስታወሻ:

 • *ቡድን 5 እና ኮምዩኒቲ ስፖንሰሮች ስፖንሰር እንዲያደርጉ የሚፈቀድላቸው በዩኤንኤችሲኣር ወይም ባሉበት ሀገር እውቅና የተሰጣቸውን ስደተኞች ብቻ ነው

 • #SAH ሳሆች ስደት በሚመስል ሁኔታ "refugee-like situation" ያሉ ግለሰቦችንም ስፖንሰር ሊያደርጉ ይችላሉ

 • ኣንድ ሰው ከኮምዩኒቲ ወይም ከሳህ ጋር ኣብሮ ካልፈረመ በስተቀር ብቻውን ሰደተኞችን ወደ ካናዳ ስፖንሰር ማድረግ ኣይችልም

 • ስደተኞችን ስፖንሰር ማድረግ የሚቻልባቸው ሁለት ተጨማሪ መንገዶች ኣሉ

 1.  Blended Visa Office-Referred (BVOR) Program and 

 2. Joint Assistance Sponsorship (JAS) Program.  ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እዚህ ይጫኑ።

 

*ሰላምታ ኢሚግሬሽን ኣገልግሎት ስፖንሰር የሚያደርግ ግለሰብም ሆነ ቡድን  የማገናኘት ስራ እንደማይሰራ ያስታውሱ

 • ስደተኞችን ስፖንሰር ለማድረግ እንዲፈቀድላቸው ከካናዳ መንግስት ጋር ስምምነት የገቡና ስደተኞች በካናዳ መኖር ሲጀምሩ የሚያግዙ ድርጅቶች  ናቸው

 • በራሳቸው ስፖ ንሰር ሊያደርጉ ይችላሉ ወይም ስደተኞችን ስፖንሰር ከሚያደርጉ በማህበረሰቡ ውስጥ ካሉ ሌሎች ጋር ኣብረው ይሰራሉ

 • ኣብዛኞቹ ሳሆች የሐይማኖት፣ የዘር፣ የማህበረሰብ ወይም የኣገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ናቸው

በየፕሮቪንሱ የሚገኙ ሳሆችን ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።

የኢሚግሬሽን አማካሪ አገልግሎት የሚያስፈልግዎት ለምን ሊሆን ይችላል?

ሳህ (SAH) ምንድን ነው?

Canada Selamta

ኤክስፕሬስ ኢንትሪ ምንድን ነው?

ኤክስፕሬስ ኢንትሪ (EE) የካናዳ ኢሚግሬሽን፣ ሬፊውጂ እና ዜግነት መስሪያ ቤት (IRRC) ከስር ለተዘረዘሩት ፕሮግራሞች የቋሚ መኖሪያ ፈቃድ ማመልከቻዎችን ለማቀናበር  የሚጠቀምበት  ኤሌክትሮኒክ ሲስተም ነው

የካናዳ የስራ ልምድ (Canadian Experience Class - CEC)

የፌደራል ልዩ ብቃት ያላቸው ሠራተኖች ፕሮግራም (Federal Skilled Worker Program - FWSP)

የፌደራል ብቃት ያላቸው ነጋዴዎች ፕሮግራም (Federal Skilled Trades Program - FSTP)

ለማመልከት ብቃቱን አሟላለው?

ልዩ ሙያ አለዎት?

እንግሊዝኛ/ፈረንሳይኛ ቋንቋ ተፈትነዋል?

(እዚህ በመጫን አሰስመንት ፎርሙን ይሙሉና ለማመልከት ብቃቱን ያሟሉ እንደሆነ ልንገልጽልዎት እንችላለን

የነጥብ አሰጣጡ የሚሰራው እንዴት ነው?

ነጥብ የሚሰጠው በእድሜ፣ በትምህርት ደረጃ፣ በቋንቋ፣ በሥራ ልምድ፣ በልዩ ችሎታ ወይም የሥራ እድል (Job offer) ማግኘት በመሳሰሉት ሁኔታዎች ላይ ተመስርቶ ነው

አጠቃላይ ሂደቱ ምን ይመስላል?

በመጀመሪያ - ፕሮፋይል ይክፈቱ
(ይህ ፕሮፋይል ከተከፈተ አንስቶ ለአንድ አመት ያገለግላል)


ማመልከቻዎ ወደ EE ፑል ይገባል


በመቀጠልም - እንዲያመለክቱ ተመርጠው ከተጋበዙ ያመልክቱ
(ግብዣው፣ ማለትም Invitation To Apply - ITA ከደረስዎት በኋላ ማመልከቻዎን ለማስገባት 60 ቀናት ይኖርዎታል)

ኤክስፕሬስ ኢንትሪ (EE)

bottom of page