የምንሰጣቸው አገልግሎቶች እና ልምዶቻችን
ከምንሰጣቸው የአገልግሎት አይነቶች ውስጥ የተወሰኑት ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል። ወደ ካናዳ መምጣት የሚቻልባቸው ከ60 የሚበልጡ መንገዶች አሉ። የሁሉም ሰው ሁኔታ የተለያየ ስለሆነ ብቃቱን የሚያሟሉ ከሆነ ለርስዎ የሚሆነውን እንዲመርጡ እናግዝዎታለን።
የትዳር ጓደኛን ማምጣት
የካናዳ ዜግነት ወይም የመኖሪያ ፈቃድ ካለዎት የትዳር ጓደኛዎን፣ የጋራ-ሕግ አጋርዎን (common-law partner) እና ልጆቻቸውን ማምጣት ይችላሉ
የቤተሠብ አባላትን ማምጣት
የካናዳ ዜግነት ወይም የመኖሪያ ፈቃድ ካለዎት የሚወዷቸውን የቤተሠብ አባላት የመኖሪያ ፈቃድ እንዲያገኙ ሊያደርጉ ይችላሉ።
የካናዳ የስራ ልምድ
በካናዳ ውስጥ ተቀጥረው ሰርተው ወይም ደግሞ ተምረው የሚያውቁ ከሆነ፣ ወይም ደግሞ እየሰሩ እና እየተማሩ የሚገኙ ከሆነ በዚህ ምድብ ውስጥ ብቃቱን ሊያሟሉ ይችላሉ።
የፌደራል የሙያ ሠራተኛ
የካናዳ መንግስት በተወሰነ ሁኔታ የሚከተሉትን ለሚያሟሉ ተመራጮች የመኖሪያ ቪዛ ይሰጣል፡ ከፍተኛ ትምህርት፣ የስራ ልምድ እና የእንግሊዝኛ ወይም የፈረንሳይኛ ቋንቋ እውቀት ላላቸው
ፕሮቪንሺያል ኖሚኒ
ብዙዎቹ አውራጃዎች ባላቸው የስራ ዕድል እና/ወይም ስደተኛው ከአውራጃው ጋር ሊኖረው በሚችል ትስስር ላይ በመመስረት የራሳቸውን ስደተኛ ለመምረጥ ከካናዳ መንግስት ጋር ስምምነት አላቸው።
የንግድ እና ኢንቬስተር ቪዛ
ካናዳ አዳዲስ ንግዶችን በማበረታታት በየአመቱ በርካታ ኢንቬስተሮችን ከአለም ዙሪያ እንደ አዲስ ካናዳዊያን ትቀበላለች። ይህ ምድብ በንግዱ ልምድ ያላቸውን እና ጠንካራ የካናዳ ኢኮኖሚ ለመገንባት ሊያግዙ ለሚችሉ የታቀደ ነው።
የቤት ውስጥ ተንከባካቢዎች
በሠራተኛ አቀጣጠር መመዘኛ መሠረት የሚፈለገውን መስፈርት የሚያሟሉ በዚህ ምድብ ማመልከት ይችላሉ
የኪውቤክ አውራጃ
ኪውቤክ በአገሪቱ ውስጥ ከሚገኙት ሌሎች አውራጃዎች ሁሉ ሰለ ኢሚግሬሽን የተለየ አሠራር ያለው አውራጃ ነው። በሌሎቹ ፕሮግራሞች ብቃቱን የማያሟሉ ስደተኞች በኪውቤክ የምርጫ መስፈርት ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ። (ይህን አገልግሎት አንሰጥም)
ጊዜያዊ የነዋሪነት ቪዛ
እነኝህ ቪዛዎች የሚሰጡት ለመጎብኝት፣ ለመማር ወይም በጊዜያዊነት ለመስራት ለሚፈልጉ ሰዎች ነው። በባለሙያ የተዘጋጀ ማመልከቻ እነዚህ ቪዛዎች ፕሮሠስ በሚደረጉበት ጊዜ ትልቅ ለውጥ ሊያመጡ ይችላሉ።
የተማሪ ቪዛዎች/ፈቃዶች
በየአመቱ ከ130,000 የሚበልጡ ቪዛዎች ከዓለም ዙሪያ ለሚያመለክቱ ተማሪዎች ይሰጣሉ።
የጎብኝ ቪዛዎች/ፈቃዶች
በየዓመቱ ከ35 ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎች ካናዳን ይጎበኛሉ። ከአንዳንድ አገሮች የሚመጡ ጎብኝዎች ወደ ካናዳ ከመምጣታቸው በፊት ቪዛ ማግኘት ይኖርባቸዋል።
LMIA/LMO እና የስራ ፈቃድ
ካናዳ በሺዎች የሚቆጠሩ የሌላ ሃገር ሰራተኞች አሏት እንዲሁም በየአመቱ ከ90 ሺህ የሚበልጡ ግለሰቦች በጊዜያዊነት በካናዳ ለመስራት ይህን ቪዛ ያገኛሉ።
STATUS OF VISA APPLICATIONS FOR PEOPLE WHOSE APPLICATIONS ARE IN-PROCESS
Whether you are our client or not, we can help you to obtain and decode a status report of your Canadian Visa application, with notes made by the officers processing your file. You can find out the exact status of your application.