top of page
በቋሚነት ከሚመጣባቸው መንገዶች ዋና ዋናዎቹ
Amharic Permanent
በጊዜያዊነት ከሚመጣባቸው መንገዶች ዋና ዋናዎቹ
Amharic temp
ስለ እኛ

ሰላምታ የኢሚግሬሽን አገልግሎት በካናዳ የንግድ ማህበራት ህግ መሰረት የተቋቋመ የካናዳ የኢሚግሬሽን አማካሪ ድርጅት ነው። የሚገኘው በካልጋሪ፣ አልበርታ ካናዳ ውስጥ ሲሆን የድርጅቱ ባለቤት እና ስራ አስኪያጅ፣ ሳይን አማኑኤል፣ ሬጉሌትድ የካናዳ ኢሚግሬሽን አማካሪ (RCIC - Regulated Canadian Immigration Consultant) እንዲሁም የካናዳ የኢሚግሬሽን አማካሪዎች ሬጉላቶሪ ካውንስል (ICCRC - Immigration Consultants of Canada Regulatory Council) አባል ናት።

የICCRC አባል በመሆኗም በኢሚግሬሽን እና ስደተኛ ጥበቃ ህግ መሰረት አንድን ግለሰብ ለማማከር እንዲሁም ወክላ ጉዳይ ለማስፈጸም እንድትችል በካናዳ መንግስት ስልጣን ተሰጥቷታል።

በካናዳ ህግ/ቢል C-35 በማናቸውም ደረጃ የሚገኝ የኢሚግሬሽን አገልግሎቶችን በክፍያ መስጠት የሚችለው ኦቶራይዝድ ረፕረዘንታቲቭ (Authorized Representative) ብቻ ነው። ኦቶራይዝድ ረፕረዘንታቲቭ የሚከተሉትን ያካትታል:

  • በICCRC በጥሩ አቋም የሚገኙ አባላት፣

  • በፕሮቪንሺያል ወይም ተሪቶሪያል የህግ ማህበራት በጥሩ አቋም የሚገኙ ጠበቃዎች

  • በጥሩ አቋም የሚገኙ የChambre des notaires du Quebec አባል የሆኑ ኖታሪዎች።

 

ስለዚህ ጉዳይ ከካናዳ መንግስት የተሰጠ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘትና ዋና ነጥቦቹን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ። ወይም የህግ/ቢል C-35 ማሻሻያ (Bill C-35: An Act to amend the Immigration and Refugee Protection Act click) ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ።

Syn Amanuel

+1 (587) 707-2989

+1 (403) 800-9850

Fax +1 (888) 927-1883

info@selamtaimmigration.com

Office hour 

Tuesday          9 am – 5 pm

Wednesday     9 am – 5 pm

Thursday        9 am – 5 pm

Friday              9 am – 1 pm

 

Monday, Saturday, Sunday and Statutory holidays -  Closed

ሳይን ኣማኑኤል
Syn Amanuel
በመስኩ ያለን ልምድ

ሳይን አማኑኤል በእንግዳ ተቀባይነት፣ በአስተርጓሚነት፣ አዲስ የመጡ እንግዶችን በማገዝና በማላመድ በሚሰሩ የተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ እንዲሁም በግል በፈቃደኛ ሰራተኛነት ወደ ሁለት አስርተ አመታት  የሚጠጋ ልምድ አላት።

ከምታውቃቸው ሰዎች ውስጥ አብዛኞቹ ስደተኛ የነበሩ፣ ጥገኝነት ጠያቂዎች እና በተለያዩ የስደት ምድቦች ወደ ካናዳ የመጡ ግለሰቦች ናቸው።

በ2016 የኢሚግሬሽን ኮንሰልታንት ዲፕሎማ ማግኘቷ የካናዳ ኢሚግሬሽን እንዴት እንደሚሰራ እንዲሁም ውጤታማ የሆኑ ከ60 የሚበልጡ ወደካናዳ  የሚመጣባቸው መንገዶችን በተመለከተ ጥልቅ የሆነ ግንዛቤ አስጨብጧታል።

ሳይን አማኑኤል ከ2016 ጀምሮ ረጉሌትድ የካናዳ ኢሚግሬሽን አማካሪ በመሆን በዚሁ ስራ ላይ ተሰማርታ ትገኛለች።

 

የትምህርት ማስረጃዎች:

  • የኢሚግሬሽን ኮንሰልታንት - ዲፕሎማ (Ashton College)

  • የስደተኛ ስፖንሰርሺፕ የስልጠና መርሃግብር - ሰርተፊኬት -(RSTP)

  • ቃለ መሃላ አስፈጻሚ - ሰርተፊኬት (Commissioner of Oaths)

የፈቃደኛ አገልግሎት:

  • Board of Directors at International Ave BRZ, Calgary (2019-Current) 

  • CIWA (ካልጋሪ፣ አልበርታ) 2008 - 2011

  • SISO (ሃሚልተን፣ ኦንታሪዮ) 2003 -2006

  • New Comers (ሴይንት ጆን፣ ኒውብረንስዊክ) 2001 – 2003

የኢሚግሬሽን አማካሪ አገልግሎት የሚያስፈልግዎት ለምን ሊሆን ይችላል?

ተጨማሪ መረጃዎች

ስደተኞች በግል  ስፖንሰር ሊደረጉባቸው የሚችሉባቸው ሶስት መንገዶች 

  1. ቡድን 5 - በአንድ ከተማ ውስጥ የሚኖሩና ስደተኛውን (ከነቤተሰቡ) ለአንድ አመት ለመደገፍ የሚያስችል የገንዘብ አቅም ያላቸው የካናዳ ዜግነት ወይም የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ኣምስት ሰዎች *

  2. ኮምዩኒቲ ስፖንሰር - ማናቸውም የተመዘገቡ የካናዳ ድርጅቶች ወይም የንግድ ድርጅቶች (ኢንኮርፖሬትድ የሆኑም ሆነ ያልሆኑ) ስደተኛውን (ከነቤተሰቡ) ለአንድ አመት ለመደገፍ የሚያስችል የገንዘብ አቅም ያላቸው *

  3. ሳህ (SAH Sponsorship Agreement Holder) - ሳህ ስደተኞችን ስፖንሰር ለማድረግ እንዲፈቀድላቸው ከካናዳ መንግስት ጋር ስምምነት የገቡ ኢንኮርፖሬትድ ድርጅቶች ናቸው #

ማስታወሻ:

  • *ቡድን 5 እና ኮምዩኒቲ ስፖንሰሮች ስፖንሰር እንዲያደርጉ የሚፈቀድላቸው በዩኤንኤችሲኣር ወይም ባሉበት ሀገር እውቅና የተሰጣቸውን ስደተኞች ብቻ ነው

  • #SAH ሳሆች ስደት በሚመስል ሁኔታ "refugee-like situation" ያሉ ግለሰቦችንም ስፖንሰር ሊያደርጉ ይችላሉ

  • ኣንድ ሰው ከኮምዩኒቲ ወይም ከሳህ ጋር ኣብሮ ካልፈረመ በስተቀር ብቻውን ሰደተኞችን ወደ ካናዳ ስፖንሰር ማድረግ ኣይችልም

  • ስደተኞችን ስፖንሰር ማድረግ የሚቻልባቸው ሁለት ተጨማሪ መንገዶች ኣሉ

  1.  Blended Visa Office-Referred (BVOR) Program and 

  2. Joint Assistance Sponsorship (JAS) Program. ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እዚህ ይጫኑ።

*ሰላምታ ኢሚግሬሽን ኣገልግሎት ስፖንሰር የሚያደርግ ግለሰብም ሆነ ቡድን  የማገናኘት ስራ እንደማይሰራ ያስታውሱ

  • ስደተኞችን ስፖንሰር ለማድረግ እንዲፈቀድላቸው ከካናዳ መንግስት ጋር ስምምነት የገቡና ስደተኞች በካናዳ መኖር ሲጀምሩ የሚያግዙ ድርጅቶች  ናቸው

  • በራሳቸው ስፖ ንሰር ሊያደርጉ ይችላሉ ወይም ስደተኞችን ስፖንሰር ከሚያደርጉ በማህበረሰቡ ውስጥ ካሉ ሌሎች ጋር ኣብረው ይሰራሉ

  • ኣብዛኞቹ ሳሆች የሐይማኖት፣ የዘር፣ የማህበረሰብ ወይም የኣገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ናቸው

 

በየፕሮቪንሱ የሚገኙ ሳሆችን ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ

ሳህ (SAH) ምንድን ነው?

ኤክስፕሬስ ኢንትሪ ምንድን ነው?

 

ኤክስፕሬስ ኢንትሪ (EE) የካናዳ ኢሚግሬሽን፣ ሬፊውጂ እና ዜግነት መስሪያ ቤት (IRRC) ከስር ለተዘረዘሩት ፕሮግራሞች የቋሚ መኖሪያ ፈቃድ ማመልከቻዎችን ለማቀናበር  የሚጠቀምበት  ኤሌክትሮኒክ ሲስተም ነው

የካናዳ የስራ ልምድ (Canadian Experience Class - CEC)

የፌደራል ልዩ ብቃት ያላቸው ሠራተኖች ፕሮግራም (Federal Skilled Worker Program - FWSP)

የፌደራል ብቃት ያላቸው ነጋዴዎች ፕሮግራም (Federal Skilled Trades Program - FSTP)

ለማመልከት ብቃቱን አሟላለው?

            ልዩ ሙያ አለዎት?

        እንግሊዝኛ/ፈረንሳይኛ ቋንቋ ተፈትነዋል?

(እዚህ በመጫን አሰስመንት ፎርሙን ይሙሉና ለማመልከት ብቃቱን ያሟሉ እንደሆነ ልንገልጽልዎት እንችላለን)

የነጥብ አሰጣጡ የሚሰራው እንዴት ነው?

ነጥብ የሚሰጠው በእድሜ፣ በትምህርት ደረጃ፣ በቋንቋ፣ በሥራ ልምድ፣ በልዩ ችሎታ ወይም የሥራ እድል (Job offer) ማግኘት በመሳሰሉት ሁኔታዎች ላይ ተመስርቶ ነው

አጠቃላይ ሂደቱ ምን ይመስላል?

በመጀመሪያ - ፕሮፋይል ይክፈቱ
(ይህ ፕሮፋይል ከተከፈተ አንስቶ ለአንድ አመት ያገለግላል)


ማመልከቻዎ ወደ EE ፑል ይገባል


በመቀጠልም - እንዲያመለክቱ ተመርጠው ከተጋበዙ ያመልክቱ
(ግብዣው፣ ማለትም Invitation To Apply - ITA ከደረስዎት በኋላ ማመልከቻዎን ለማስገባት 60 ቀናት ይኖርዎታል)

ኤክስፕሬስ ኢንትሪ (EE)

በሚከተሉት መንገዶች ሊያገኙን ይችላሉ

 

ሥልክ: +1(587) 707-2989 ሞባይል

          +1(403) 800-9850 ቀጥታ መስመር

ኢሜይል: info@selamtaimmigration.com

ይከተሉን:

 

የካናዳ ዜግነትን እና ኢሚግረሽንን በተመለከቱ ጉዳዮች ልናግዝዎት ዝግጁ ነን 

  • Facebook Social Icon
  • LinkedIn Social Icon
  • Selamta YouTube Channel
Anchor 1
bottom of page